Search

የአርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ በአምቦ ይፈጸማል

ሰኞ ጳጉሜን 02, 2018 300

ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለሕዝቦች እኩልነትና ለፍትሕ መረጋገጥ በሙዚቃ ሥራውቿ የምትታወሰው ታላቅ የኪነ-ጥበብ ባለሙያና ህያው አሻራዋን አሳርፋ ተሰናብታለች።

የአንጋፋዋ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በገዛ ኑዛዜዋ መሠረት ነገ ጳጉሜ 03 ቀን 2018 . በአምቦ ከተማ በክብር ሥነ-ሥርዓት ይፈጸማል።

አዘጋጅ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ የአርቲስቷ አስከሬን ሽኘት ነገ ከጠዋቱ 11:00 እስከ 12:00 ከኮሪያ ሆስፒታል ወደ መኖሪያ ቤቷ የሚደረግ ይደረጋል።

ከጠዋቱ 12:00 እስከ 1:00 ባለው ጊዜ ደግሞ ከመኖሪያ ቤቷ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ይወሰዳል።

የአርቲስቷ ወደጆች ጓደኞችና አድናቂዎች ነገ ከጠዋቱ 1:00 - 3:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የጀግና አሸኛኘት ካደረጉላት በኋላ ወደ አምቦ ሽኝት እንደሚደረግ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የዕድሜ ልክ ትግሏን ለሰው ልጆች ነፃነትና ለህዝብ ድምፅነት የሰጠችው አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ፣ በህይወት እያለች "ከዚህ ዓለም ስሰናበት ቀብሬ አምቦ ይሁን" ባለችው ኑዛዜ መሠረት፣ አስተባባሪ ኮሚቴው የጀግናዋን ፍላጎት በማክበር የመጨረሻ እረፍቷ በአምቦ ከተማ እንዲሆን ወስኗል።

በዜማዎቿ የሕዝብን ብሶትና ተስፋ ስታንጸባርቅ የኖረችው ይህች ታላቅ አርቲስት፣ በግል ሕይወቷም የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ እናት በመሆን መልካም ቤተሰብን ያፈራች እናት ነበረች።

በአሊ ደደፎ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: