የማንሰራራት ቀንን ስናከብር፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ በማሸጋገር ረገድ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እያከናወነ ያለው ድንቅ ተግባር የሀገራችን አዲስ የከፍታ ምዕራፍ ማሳያ ሆኖ ይገኛል።
ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የመሳብ፣ የወጪ ንግድን የማሳደግ፣ ተኪ ምርቶችን የማምረት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን የማፋጠን ታላቅ ሀገራዊ አደራቸውን በብቃት እየተወጡ ነው።
ከዚህም ባሻገር፣ እነዚህ ማዕከላት ለአስር ሺዎች ወጣቶች በተለይም ለወጣት ሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ሕይወት በተስፋ እያደሱ ይገኛሉ።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ኮርፖሬሽኑ ለ74 ሺህ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ይህም በአምራች ዘርፉ ከተፈጠረው ሀገራዊ የሥራ ዕድል 16 በመቶውን ይይዛል።
በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚፈጠር አንድ የሥራ ዕድል ለተጨማሪ ሁለት ዜጎች ቀጥተኛ ያልሆነ የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ በምግብ፣ በትራንስፖርት፣ በቤቶች አከራይነትና በደኅንነት ዘርፎች የበርካቶች የገቢ ምንጭ ሆኗል።
ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝቧ ዕድሜው ከ30 ዓመት በታች ለሆነው ሀገራችን፣ እነዚህ ፓርኮች የሥራ ቦታዎች ብቻ ሳይሆኑ ወጣቶች ከዓለም አቀፍ አሠራሮች ጋር የሚላመዱበትና የነገ የኢንዱስትሪ መሪዎች ሆነው የሚቀረጹበት የማንሰራራት ማዕከላት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: