Search

ዓባይ በጣና ላይ የቀለደበት ዘመን አበቃ፤ በመደመር ትውልድ የተቀየረው ተሪክ

ሰኞ ጳጉሜን 02, 2018 141

ኢትዮጵያውያን 2018 . የተቀበሉት በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም የተጻፈ፣ የትውልዶችን ሕልም ዕውን አድርገው ነው - ለዘመናት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስመረቅ።

የሕዳሴ ግድብን ዋጋ ለመረዳት ያለፍንበትን የእሾህ መንገድ ማስታወስ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት በራሷ አቅም አትጨርሰውም ያሉ ብዙዎች ነበሩ።

የገንዘብ ድጋፍ እንዳይገኝ በሮች ሲዘጉ፣ ኢትዮጵያውያን ግን ከደመወዛቸው፣ ከእርሻቸው፣ ከንግዳቸው እና ከዕለት ጉርሳቸው እየቀነሱ ድንጋይ በድንጋይ ላይ አነበሩ።

ጫናዎች ከምሥራቅም ከምዕራብም መጡ። የዲፕሎማሲ ማዕበሎች፣ የፖለቲካ እገዳዎች፣ የደኅንነት ስጋቶች... ነገር ግን ይህ ትውልድ አልተንበረከከም።

ይህ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ደሙ እና ላቡ የገነባው የነጻነት ሁለተኛ ማረጋገጫ ነው።

2018 . ላይ ስንደርስ ሁሉ ፈተና ወደ ድል ተቀየረ። ግድቡ ተጠናቀቀ፤ ተመረቀ፤ በይፋም ሥራ ጀመረ። ይህ የሥነ-ልቦና የበላይነት እና የጽናት ትልቅ ምሥክርነት ነው።

ለዘመናት ኢትዮጵያን ሲፈትናት የነበረው ትልቁ ማነቆ የኃይል እጥረት ነበር። ፋብሪካዎች በኃይል እጥረት ምክንያት ሙሉ አቅማቸውን አይጠቀሙም፤ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችም በኃይል አቅርቦት መዘግየት ይስተጓጎሉ ነበር።

 

የሕዳሴው ግድብ ሥራ መጀመር የሀገር ውስጥ የኃይል እጥረትን አቃልሏል። አሁን ፋብሪካዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አምራች ድርጅቶች በሙሉ አቅማቸው እንዲሠሩ አድርጓል።

የኢንዱስትሪ አብዮትን አፋጥኗል። አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ማለት አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች፣ አዳዲስ የፋብሪካ በሮች መከፈት እና ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል መፈጠር ማለት ነው።

የሕዳሴው ግድብ ጥቅም ለኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ለምሥራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ታላቅ ብሥራት ይዞ መጥቷል።

ኢትዮጵያ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ባለቤት መሆኗ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ መስመር የማስተሣሠር አህጉራዊ ራዕይዋን አረጋግጣለች።

ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን ንጹሕ እና አስተማማኝ የታዳሽ ኃይል በመጠቀም ላይ ይገኛሉ።

ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላታል።

የቀጣናው ሀገራት የኢንዱስትሪ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ የኃይል ማዕከልነት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖም ከፍ ብሏል።

በኤሌክትሪክ የተሳሰረ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት የጋራ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ለሰላም በጋራ ይቆማሉ።

ዓመቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ልዩ ዓመት ሆኖ በታሪክ መዝገብ ላይ ተመዝግቧል።

የትውልዱ ተስፋ እውን የሆነበት፣ ኢትዮጵያ የራሷን ታሪክ በአዲስ ምዕራፍ የጻፈችበት ዓመት ነው።

"ዓባይ በጣና ላይ እንዴት ቀለደበት፣ ለአንድ ቀን ነው ብሎ ዘንት ዓለም ሄደበት" ይባል ነበር። ይህን የመደመር ትውልድ "ዓባይ በጣና ላይ እንዴት ቀለደበት፣ ለአንድ ቀን ነው ብሎ ጉባ ላይ ከተመበት" በሚል ቀይሮታል።

በንብረቴ ተሆነ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: