ከዕዳ እና ኪሳራ ወደ 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ! የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያስመዘገበው አስደናቂ የፋይናንስ ተዓምር እንዴት ሊሆን ቻለ?
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 ዓ.ም 39.5 ቢሊዮን ብር ማትርፉን ይፋ አድርጓል። ይህ ስኬት ተቋሙ ከነበረበት ከባድ የፋይናንስ ውድቀት ተላቅቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ጤናማ የፋይናንስ ደረጃ የተሸጋገረበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ከስድስት ዓመት በፊት ተቋሙ የነበረበት ሁኔታ እጅግ አስደንጋጭ ሲሆን፣ የበጀቱን 89 በመቶ በሀገር ውስጥ እና ከውጭ በሚያገኘው ብድር ይሸፍን ነበር።
ይህንን ግዙፍ ኪሳራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ የቀየረው ምንድን ነው?
መንግሥት ያከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና የሥራ አመራር ቦርዱ የሰጧቸው አቅጣጫዎች፣ እንዲሁም የተቋሙ ማኔጅመንት የወሰዳቸው ቁርጠኛ ተቋማዊ ሪፎርሞች የፋይናንስ ጤናማነቱን በዘላቂነት አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋማዊ ሪፎርም እና ትክክለኛ አመራር ከተጨመረበት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኪሳራ ወጥተው ወደ ግዙፍ አትራፊነት መሸጋገር እንደሚችሉ ትልቅ ማረጋገጫ ሆኗል።
በንብረቴ ተሆነ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: