በማንሰራራት ቀን ሀገራዊ ተስፋችንን ስናድስ፣ ኢትዮጵያ ለዘመናት በአንድ የኃይል ምንጭ ላይ ብቻ ትደገፍ የነበረችበትን ታሪክ ሙሉ በሙሉ ቀይራ ወደ አዲስና ዘመናዊ የኃይል ዘመን ተሸጋግራለች።
በታዳሽ የኃይል ዘርፍ የተቀመጠው ሀገራዊ ራዕይ በጽናት ወደ ተግባር እየተቀየረ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህም የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ከመቀየር ባለፈ ሀገራችንን የምሥራቅ አፍሪካ ዋና የንጹሕ ኃይል ማዕከል አድርጓታል።
ይህ የኃይል ማንሰራራት የሀገራችንን የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ መሠረት በጽኑ እየደገፈው ይገኛል።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 5,150 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጨት በመጀመሩ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኃይል አቅም ከእጥፍ በላይ እንዲያድግ አድርጎታል።
እንደ አሸጎዳ፣ አዳማ፣ አይሻ እና አሰላ ባሉ የነፋስ ኃይል ፕሮጀክቶች ተጨማሪ 504 ሜጋ ዋት ማግኘት መቻሉ ደግሞ ሌላኛው ተጨማሪ አቅም ነው።
በተጨማሪም የጂኦተርማል እና የሶላር አማራጮች ተስፋፍተው ከዋናው የግሪድ መስመር ርቀው የሚገኙ በርካታ የገጠር መንደሮችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ተቋማት ብርሃን እንዲያገኙ አድርገዋል።
ይህ የታዳሽ ኃይል ልማት ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ኃይል ከማቅረቡ ባሻገር፣ ከአካባቢ በካይ ጋዝ የጸዳ አረንጓዴ ኢነርጂን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በታዳሽ የኃይል አማራጮች ያረጋገጠችው ይህ ተአምር ሀገራችንን ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ እድገት የሚያሸጋግር ታሪካዊ የማንሰራራት ማሳያ ነው።
በንብረቴ ተሆነ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: