Search

የኅብረት ተዓምር፦ የሺህ ዓመታት ቁጭት ማሰሪያው እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓድዋ

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 43

ጳጉሜን 4 ቀን 2017 . በኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብ ላይ በወርቃማ ቀለም የተጻፈች ታላቅ ዕለት ነች። ያቺ ቀን ኢትዮጵያን የሺህ ዘመናት ቁጭታቸውን ፍሬ ያዩባት ሆና ስትዘከር ትኖራለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በይፋ ሲመረቅ በምረቃው ዋዜማ ምሽት የታየው ክስተት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ልብ የነካ እና ጥልቅ የስሜት መነቃቃትን የፈጠረ ነበር።

በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ያነቡት የደስታ ዕንባ የመላው ሕዝብ የዘመናት ስቃይ፣ መገለል እና ጥልቅ ቁጭት በድል የተተካበት ታሪካዊ መግለጫ ነው።

ዕንባ ለዘመናት ሀብቷን ይዞ ሲፈስስ የኖረውን ዓባይን የመግራት ሕልም እውን መሆኑን ያበሰረ፣ የትውልዶች ጥረት እና መሥዋዕትነት ፍሬ ማፍራቱን ያረጋገጠ ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው አጋጣሚ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በምረቃው ዕለት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር፣ ሕዳሴ ግድብ የትናንት ቁጭት ማሰሪያ እና የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።

ለሺህ ዓመታት ዓባይ እግር እንጂ አፍ እንዳልነበረው እና ኢትዮጵያውያን ለወንዙ ሲያወሩለት እንደኖሩ አስታውሰው፣ ዛሬ ግን ዓባይ ራሱ በጉባ ምድር ላይ በኃይል ማመንጨት አፍ አውጥቶ መናገር መጀመሩን አስረድተዋል።

ይህ ስኬት ኢትዮጵያ በገዛ እጇ የታሪክ ዕዳዋን መክፈሏን የሚያሳይ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ የትኛውም ምድራዊ ኃይል የኢትዮጵያን የማንሰራራት እና የብልጽግና ጉዞ ማቆም እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሙሉ እምነት ተናግረዋል።

የምረቃው ሥነ-ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ በዕለቱ የተገኙት የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ያደረጉት ንግግር የዚህን ድል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትርጉም በግልጽ አመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይህን ታላቅ ፕሮጀክት የጥቁር ሕዝቦች ድል አድርገው በመሰየም፣ "21ኛው ክፍለ ዘመን የምሕንድስና ዓድዋ" ሲሉ ገልጸውታል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የፋይናንስ ተቋማት እጃቸውን በሰበሰቡበት እና ፕሮጀክቱ አይሳካም ባሉበት ወቅት፣ ሕዝቡ በራሱ አቅም 4 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር በማሰባሰብ ታሪክ መጻፉን አድንቀዋል።

የካቲት 1888 . የተጎናጸፍነው የዓድዋ ድል ለአፍሪካውያን የነጻነት ፋና እንደበራ ሁሉ፣ ሕዳሴ ደግሞ በራሳችን አቅም የመልማት እና የመበልጸግ ብቃታችንን ያስመሰከርንበት ዳግማዊ ዓድዋ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የዚህ ታሪካዊ አሸናፊነት ምስጢር እና ቁልፍ መሣሪያ የኢትዮጵያውያን የማይበገር ኅብረት ነው።

ከገበሬው እስከ ተማሪው፣ ከሠራተኛው እስከ ነጋዴው እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ሳይቀሩ በላባቸው፣ በደማቸው እና በሀብታቸው በአንድነት በመቆማቸው ይህ ተአምር እውን ሊሆን ችሏል።

ኢትዮጵያውያን በአንድ ዓላማ እና በጽኑ ሕሊና ከተነሡ እና ኅብረታቸውን ካጠናከሩ፣ በፊታቸው የሚቆምም ሆነ ጉዟቸውን የሚያስተጉል ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ይህ ፕሮጀክት ሕያው ምስክር ነው። የውጭ ጫናዎች እና ተደራራቢ ፈተናዎች በሙሉ በሕዝባዊ ጽናት እና አንድነት ፊታቸውን አጥፈዋል።

በመሆኑም በሕዳሴ ግድብ የተረጋገጠውን ይህንን ድንቅ የኅብረት እና የሕዝባዊ አቅም መንፈስ በቀጣዮቹ የልማት እና የዕድገት ምዕራፎች ላይ በበለጠ ቁርጠኝነት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

በቀጣይ በጉባ ተበስረው የተጀመሩ ግዙፍ ሜጋ-ፕሮጀክቶችን ከፍፃሜ ለማድረስ እና ሀገራችንን ወደ ተሟላ ብልጽግና ለማሸጋገር ትናንት በጉባ ያስመሰከርነውን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዛሬም ለቀጣይ ስኬቶቻችን መሠረት ልናደርገው ይገባል።

አንድነታችን የጥንካሬአችን ምንጭ፣ ኅብረታችን ደግሞ የማሸነፋችን ማረጋገጫ ሆኖ ይኖራል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: