Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 37

አዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ሀገር በቀል እሴቶችን በተግባር በማዋል በመላው ክፍለ ከተሞች፣ ወረዳዎች እና በማዕከል ደረጃ ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባዋ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ጧሪ እና ደጋፊ ለሌላቸው፣ ለማኅበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ ለአረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የተደረገ የፍቅር ሥጦታ መሆኑን አብራርተዋል። ድርጊቱም አብሮነትን፣ መረዳዳትን እና ሰው ተኮር ተግባራትን ባህል በማድረግ ማኅበራዊ ትሥሥርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ይህ ተግባር ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ያለው ለሌለው እንዲያካፍል እየተደረገ ያለ የዘወትር በጎ ሥራ አካል መሆኑን ያነሡት ከንቲባዋ፣ በዛሬው ዕለት የተደረገው ማዕድ ማጋራትም ምግብን ከመመገብ ባለፈ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ፍቅርን፣ አብሮነትን እና አክብሮትን ለከተማዋ ነዋሪ ማካፈል ጭምር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

"መስጠት አያጎድልም" በሚል እሳቤ ካላቸው ላይ ቀንሰው በከተማዋ ለተካሄደው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለሃብቶች፣ ማኅበራት እና ልበ-ቀና ግለሰቦች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አዲሱ ዓመትም የፍቅር፣ የሰላም እና በትጋት ሰርቶ የመለወጥ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: