Search

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት የኅብር ቀንን አስመልክቶ ለ6 በጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ አደረገ

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 87

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት የኅብር ቀንን አስመልክቶ ከመላው የተቋሙ ሠራተኞች የተሰበሰቡ ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የሚያገለግሉ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እንዲሁም የንጽሕና መጠበቂያ፣ ምግብ ነክ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ለስድስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አድርጓል።

ድጋፉ ለአበበች ጎበና የሕፃናት እንክብካቤ እና ልማት ማኅበር፣ ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት፣ ለአንከር ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት፣ ለጆይንት ቪዥን አካዳሚ፣ ለኦፕን ፊውቸር ኢትዮጵያ እና ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት የተደረገ ሲሆን፣ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት ተጨማሪ 200 ሺህ ብር የገንዘብ ዕገዛ ተደርጓል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት 300 አባላትም የኅብር ቀንን አስመልክቶ ደም በመለገስ የወገኖቻቸውን ሕይወት በመታደግ ጥረት የድርሻቸውን ማበርከታቸውን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደዚህ ዓይነት ሰብዓዊ ተግባሮች እና ማኅበራዊ ድጋፎች የተቋሙን ሕዝባዊነት የሚመሰክሩ እንደሆነ ዕገዛ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገልጸዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ተወካዮችም ማኅበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት በተለያዩ ጊዜያት ከተቋሙ ሠራተኞች ቁሳቁስ እና ገንዘብ በማሰባሰብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን እና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: