Search

የኢትዮጵያ የታላቅነት ሕልም ወደ ሜጋ እውነታ የሚሸጋገርበት 2019 ዓ.ም

ዓርብ መስከረም 01, 2019 120

የጳጉሜን ቀናት ተቆጥረው አልቀው የመስከረም መልክ በአበባ ሲገለጥ እና አዲሱ 2019 . በይፋ ሲጠባ በየቤቱ አዲስ ተስፋና ደስታ ይፈነጥቃል።

አዲሱ ዓመት የዘመን ሽግግር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለዘመናት ዓልማ ያስቀመጠቻቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶች ወደ ተጨባጭ እምርታ የሚያሸጋግርበት እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባበት አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው።

ኢትዮጵያ አዲሱን 2019 . የተቀበለችው በበዓል ድምቀት ብቻ ሳይሆን ምድር ላይ በሚታዩ ግዙፍ የልማት እውነታዎች እና 24 ሰዓት የትጋት ሥራ ነው።

ለዘመናት በበጀት እጥረት እና በሚጎተቱ የጊዜ ሰሌዳዎች ሰበብ ተስፋ ያስቆርጡ የነበሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ዛሬ ላይ ሀገራዊ ተስፋ ማነቃቂያ እና የመጻኢዋ ኢትዮጵያ የማዕዘን ድንጋይ ሆነዋል።

ከአፍሪካ ግዙፉ እና የአቪዬሽን ዘርፉን አቅጣጫ የሚቀይረው፣ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ግንባታ አንዱ ማሳያ ነው።

ግንባታው እየተፋጠነ ያለው እና 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክት በአዲሱ ዓመት ታሪካዊ እምርታን የሚያሳዩ ናቸው።

እነዚህ ግዙፍ የልማት ጥረቶች በአዲሱ 2019 . ሙሉ በሙሉ አቅማቸውን ገልጠው ወደ ሥራ ሲገቡ በዜጎች ዕለታዊ ሕይወት እና በብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ አብዮታዊ ለውጥ ያመጣሉ።

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ ትራንዚት እና የአቪዬሽን ዋና ማዕከልነቷን ሲያጎለብት፣ የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ደግሞ ለኢንዱስትሪዎች፣ ለኤክስፖርት እና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የማያቋርጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል።

በተለይም በሶማሌ ክልል የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ወደ ማምረት ምዕራፍ ሲሸጋገር፣ ለሀገር ውስጥ ማዳበሪያ እና ኃይል ምርት በመዋል የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በዘላቂነት ከመቅረፉ ባሻገር የዜጎችን የመግዛት አቅም ያጎለብታል።

ይህ የመጻኢ ዕድል ተስፋ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደ ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ከፍታ የሚያሸጋግር እውነተኛ አድማስ ነው።

ከበዓል ደስታ፣ ከዕጣን እና ከአበባው ሽታ ባሻገር በኮይሻ ተራሮች፣ በቢሾፍቱ ሜዳዎች እና በሶማሌ ክልል የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ቦታዎች የሚከናወነው የጽናት ተአምር አዲሱን 2019 . በሥራ ተቀብለን በሥራ የምናሳልፈው ሀገራዊ ወቅት መሆኑን ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያ አዲሱን 2019 . በሥራ ተቀብላለች፤ በሥራም ታሳልፈዋለች። የባለፉት ዓመታት ጥረት፣ ዕቅድና ሙዓለ ንዋይ ፍሬ የሚያፈራበት፣ የተጀመሩት ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የታሪክ አካሄድ በሚቀይር እምርታ የሚደመደሙበት የብልጽግና እና የሀገራዊ ከፍታ ዘመን ይሆናል።

በሃና ምንዳሁን

.

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: