አባል እና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ የተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ በማለም የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን አረጋገጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ፣ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትሥሥርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በአዲስ አበባ የሚካሄደው 32ኛው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዝበዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: