በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ አሜክስ ስታዲየም አቅንቶ ብራይተንን የገጠመው አርሰናል 3 ለ 0 ተሸንፏል።
ሻምፒዮኑ አርሰናል በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተረታበት ጨዋታ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ፓስካል ግሮስ እና ቻራላምፖስ ኮስቱላስ በመጀመሪያው አጋማሽ፣ እንዲሁም ኬማ አንድሬስ በሁለተኛው አጋማሸ ከመረብ አሳርፈዋል።
በዚህም ያለፈውን የውድድር ዓመት የመጨረሻ ሳምንታት ጨምሮ አርሰናል በዘጠኝ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የማሸነፍ ጉዞ ዛሬ አብቅቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ከሳምንት በፊት 12 ነጥብ ይዞ በግብ ክፍያ በመብለጥ የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት ከሲቲ ተረክቦ የነበረው አርሰናል፣ መሪነቱን ዳግም የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታውን በነገው ዕለት በሚያደርገው ማንቸስተር ሲቲ ተነጥቋል።
125ኛ ዓመት የምስረታ በአሉን እያከበረ የሚገኘውና ከቀናት በፊት ማንቸስተር ዩናይትድን ከካራባኦ ዋንጫ ያሰናበተው ብራይተን በውድድር ዓመቱ 3ኛ ድሉን ማሳካቱን ተከትሎ 10 ነጥብ በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: