ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣ "ግዙፍ እና እያደገ ያለ ኢኮኖሚ እንደመሆናችን መጠን፣ አስተማማኝ እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ተደራሽነት ያስፈልገናል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ዓላማዋን በሰላማዊ እና በድርድር ላይ በተመሠረቱ መንገዶች ከዳር ለማድረስ መሥራቷን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
የዚህ ጥረት ዋና ዓላማም የንግድ ወጪን መቀነስ፣ የላቀ የመቋቋም አቅምን መገንባት እና የጋራ ብልጽግናን ማረጋገጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: