Search

ኢትዮጵያ በብሪክስ ያገኘችው ስትራቴጂያዊ ዕድል

እሑድ መስከረም 03, 2019 121

ከተመሠረተ 20 ዓመቱን ያስቆጠረው የብሪክስ ጥምረት፣ ይበልጥ የተደራጀ፣ ፍትሐዊ እና አሳታፊ ማዕቀፍ ለመገንባት በሚያደርገው አዲስ የሽግግር ጉዞ የዓለም አቀፉን የኃይል ሚዛን በአዎንታዊ መልኩ እየቀየረው ይገኛል።

በዚህ ታሪካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ ቁልፍ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አዲስ ዕድል መፍጠር ችላለች።

ጥምረቱ አካታች የዓለም አቀፍ አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚከተለው መርህ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ እና የንግድ አሠራር ውስጥ ያላትን ተጽዕኖ በከፍተኛ ደረጃ ያጎለብተዋል።

ይህም ከፖለቲካዊ ጫና ነፃ በሆነ እና እኩልነትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዓለም አቀፍ የብድር እንዲሁም የኢንቨስትመንት መድረኮች ላይ ጠንካራ አጋርነት እንድትገነባ ያስችላታል።

በተለይም 130 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያላት እና ለአፍሪካ ሰፊ ገበያ ትልቅ መግቢያ በር የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በጥምረቱ ውስጥ ያላት ንቁ ተሳትፎ የጋራ ተጠቃሚነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

በሌላ በኩል ይበልጥ የተደራጀው የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል ሽግግር የጀመረቻቸውን ስኬቶች ለማሳደግ የጎላ የቴክኖሎጂ ምንጭ ይሆንላታል።

ሀገራችን በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ሉዓላዊነት እና በግብር እና ልማት ያስመዘገበቻቸውን አመርቂ ውጤቶች ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

ከተለያዩ የጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር የሚፈጠረው የካፒታል ፍሰት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሰፋ የገበያ ትስስር፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማጠናከር ሀገራዊ የልማት ግቦችን ለማፋጠን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ይጥላል።

የብሪክስ ጥምረት በሁለተኛው አስርት ዓመት የያዘው አካታች የትብብር አቅጣጫ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እና የዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በማሳደግ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ከፍታ እንድትቀዳጅ የሚያደርግ ስትራቴጂካዊ አጋጣሚ ነው።

በሀና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: