Search

ብሪክስ ከሌሎች ባህላዊ የዓለም ጥምረቶች በምን ይለያል?

እሑድ መስከረም 03, 2019 130

ብሪክስን ከሌሎች ባህላዊ የዓለም ጥምረቶች ልዩ የሚያደርገውና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ማዕከል የሚያደርገው ዋናው ምክንያት የአዳጊ ሀገራትን እውነተኛ አቅም እና የጋራ ዕድገት ማዕከል ያደረገ መሆኑ ነው።

በዚሁ ምክንያት ጥምረቱ የዓለምን 50 በመቶ ሕዝብ እና 40 በመቶ በላይ የዓለም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርትን የሚወክል ግዙፍ ኃይል ለመሆን በቅቷል።

ብሪክስ በአንድ ወገን የበላይነት ላይ የተመሠረተውን የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት በመቀየር፣ አዳጊ ሀገራት እኩል ድምፅ እና ተፅዕኖ እንዲኖራቸውኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ አቋቁሞ በመሥራት ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ጥምረቱ በአባል ሀገራቱ መካከል የንግድ መሰናክሎችን ለማስወገድ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራን ለማስፋፋት እንዲሁም አዳዲስ የንግድ አጋርነቶችን ለመፍጠር ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው።

ዓላማውም በደቡብ ክፍለ ዓለም ሀገራት መካከል አካታች የሆነ የባለብዙ ወገን ትብብር በመፍጠር፣ እርስ በርስ እንዲደጋገፉ በማስቻል እና ድምፃቸውን በማስተጋባት የጋራ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው።

በጥቅሉ ብሪክስ የጥቂቶች መድረክ ሳይሆን፣ የብዙኃን አባል ሀገራትና ሕዝቦቻቸው የጋራ ዕድገት ሞተር ነው ለማለት ይቻላል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: