በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ 1 ለ 0 በማሸነፍ አራተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
ፊል ፎደን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ላይ ጥፋት ፈፅሟል ተብሎ በቀይ ካርድ ከሜዳ በተሰናበተበት ጨዋታ፣ የማንቸስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ 60ኛው ደቂቃ ላይ ኤርሊንግ ሃላንድ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ 12 ነጥብ የሰበሰበው ሲቲ በአርሰናል በግብ ክፍያ ተበልጦ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ከአራቱ ጨዋታዎች ለ2ኛ ጊዜ የተሸነፈው ማንቸስተር ዩናይትድ 13ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: