Search

የመደመር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች በማሰባሰብ የሕዝብን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እሑድ ጥቅምት 01, 2019 54

የመደመር መንግሥት ሁሉንም ሀገራዊ እና አካባቢያዊ አቅሞች በማሰባሰብ የሕዝብን የላቀ እና ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት እና ከነዋሪዎች ጋር በመሆን የማኅበረሰብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል።

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሙሉ ጤንነቱ የተጠበቀ እና አምራች ትውልድ ለመገንባት በከተማዋ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ጠቁመው፣ የከተማው ነዋሪ እነዚህን የመሠረተ ልማት አውታሮች ዘወትር በአግባቡ እና በባለቤትነት ስሜት ሊጠቀምባቸው እንደሚገባ መክረዋል።

በስፖርቱ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶች እና የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያስቆም ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል እንደሌለም አጽንዖት ሰጥተው የተናገሩት።

“የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የከተማችንን ዘላቂ ልማት እና ሰላም አጽንቶ ለማስጠበቅ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በጋራ እና በትብብር ሊሠራ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

#የመደመርመንግሥት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: