Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ይካሄዳ

ሓሙስ ኅዳር 17, 2019 166
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ይካሄዳል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 በጀት ዓመት የመንግሥት ዕቅድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅቱ ፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡትን የመንግሥት ዕቅድ መነሻ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን አቅጣጫዎች በግልጽ እንደሚያስቀምጡም ይጠበቃል፡፡
በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችንም ያብራራሉ፡፡
ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሁሉም የዶትስሪም እና መደበኛ የሥርጭት አማራጮች የጉባኤውን ሂደት በቀጥታ ሥርጭት እንደሚያስተላልፍ እየገለጽን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: