የ12ኛው የጣና ፎረም አካል የሆነው እና በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ቀጣና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የልዩ መልዕክተኞች የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
12ኛው የጣና ፎረም "አፍሪካን ወደ ሰላም የሚወስዱ መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦ ፖለቲካዊ ሽግግር" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬን ጨምሮ ለቀናት ቀናት ቆይታ ያደርጋል።
ፎረሙ የአፍሪካ ሀገራት የቀድሞ መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ልዩ መልዕክተኞች ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን በአፍሪካ የሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረክ የመፍትሔ አቅጣጫዎች የሚቀመጡ ይሆናል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ አጋርነት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት መድረክ ነው።
በሳሙኤል ወርቃየሁ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: