Search

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኞ ጥቅምት 23, 2019 60

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 360 ወንዶች፣ 4ቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ፣ ከተመላሾች መካከል 18ቱ ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሠራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ112 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም ገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: