አዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠች፣ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እውን እያደረገች እና የከተሜነት ጉዞዋን እያፋጠነች ትገኛለች።
ከተማዋ በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በ24/7 የሥራ ባህልን በመተግበር ለዜጎች የቤት ልማት አቅርቦትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ላይ የአቅርቦት እና የአሠራር ለውጥ በማድረግና የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን በመቅረጽ በመንግሥት እና በግል አጋርነት፣ በበጎ-ፈቃድ፣ በግል ባለሀብቶች (በሪልስቴት፣ በግል እና በማህበር አልሚዎች ከቤት ግንባታ ወደ ቤት አቅርቦት መሸጋገር መቻሏ ተገልጿል።
በዚህም አዲስ አበባ ለነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ ቀዳሚ ግብ አድርጋ በመሥራት ላይ እንደምትገኝ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አመላክቷል፡፡
ከተማዋ ቤቶችን አልምታ ከማቅረብ በሻገር የተገነቡ ቤቶች የሕብረተሰቡን ማህበራዊ መስተጋብር እና አብሮነትን በሚያጠናክሩ አሠራር የተቃኙ በመሆናችው፣ የጋራ መገልገያዎች፣ የስፖርት ማዘውትሪያ ስፍራዎችን፣ የህፃናት መጫወጫ፣ አከባቢውን ጽዱ እና ወብ በማድረግ የተቀናጀ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትና የጋራ አስተዳዳር እንዲኖራችው ተደርገው በጥንቃቄና በጥራት የተገነቡ በመሆናቸው ለነዋሪዎች ምቹ መሆን ችላለች፡፡
በተለይም ለልማት ተነሺዎች፣ ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሀገር ባለውለታዎች ቅድሚያ በመስጠት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ ሁሉንም አይነት የቤት አማራጮች በሽያጭ፣ በኪራይ፣ በቁጠባ (በረጅም ጊዜ ክፍያ) እና መክፈል ለማይችሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያማከለ አካታች የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት በመተግብር ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ከተማዋ የምታከናወነው ሰው ተኮር ተግባር በዓለም መድረክ ሰሟ ከፍ ብሎ እንዲነሳ ብሎም እውቅና እና ምስጋና እንዲቸራት ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: