Search

“በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ እና በመሰል የጥፋት ቡድኖች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እየተመዘገበባቸው ነው”- የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሰኞ ጥቅምት 23, 2019 57

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በወቅታዊ የልማት ዕቅዶች አፈጻጸም እና በክልሉ የፀጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በክልሉ የፀጥታ እና የሕግ ማስከበር ሥራዎችን አስመልክቶ እንደገለጹት፣ በኦነግ ሸኔ እና በመሰል የጥፋት ቡድኖች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እየተመዘገበባቸው ይገኛል ብለዋል።

ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በክልሉ በሚገኘው በአርሲ፣ ሲርካ ወረዳ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረት መውደሙን እና ዜጎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ በተሠራ ኦፕሬሽን 73 የጽምዶ አባላት በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቁመዋል።

መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንዲሁም የምግብ፣ የጤና እና የቁሳቁስ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የአጭር ጊዜ የልማት ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፣ ዕቅዱ የኢትዮጵያን የብልጽግና ዘመን ለማረጋገጥ ከተዘጋጀው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል።

በሂደቱም የኢኮኖሚ ዕድገትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማድረስ የኦሮሚያን እና የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኃይሉ አክለውም የቀጣይ ዓመታት የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ፣ በሰነዱ መሠረት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ መደገፍ፣ ሁሉንም ኅብረተሰብ ማሳተፍ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ እና በዕውቀት እና በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ መሆን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የክልሉ ሕዝብ አንዳንድ አካላት ከሚለቅቁት የተሳሳተ መረጃ እና የፈጠራ ወሬዎች ራሱን እንዲጠብቅ፣ እንዲሁም የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ያለው የወንድማማችነት እና የአብሮነት እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

በሳዳት መሐመድሳኒ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: