Search

ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን እንዲያሳኩ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶችን ውጤታማነት ማሳደግ አስፈላጊ ነው-ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 79

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ከCOP31 ጎን ለጎን “ባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች፡ ለተሻለ ተደራሽነትና ለላቀ ተጽዕኖ በጋራ መሥራት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ፣  ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት፣ እንዲሁም ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን (climate priorities) እንዲያሳኩ በመደገፍ ረገድ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶችን ውጤታማነት ማሳደግ ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: