Search

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከታዳጊ ሀገራት (LDCs) ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ማክሰኞ ኅዳር 01, 2019 86

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 31 ጎን ለጎን ከታዳጊ ሀገራት (LDCs) ቡድን ሊቀመንበር እና የቲሞር-ሌስቴ አምባሳደር አዳኦ ሶአሬስ ባርቦሳ ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በተካሄደው በዚህ ውይይት ሁለቱ ወገኖች የታዳጊ ሀገራትን ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የኮፕ አጀንዳዎች እና ለCOP32 በሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወደ COP32 በሚደረገው ዝግጅት ሂደት ከታዳጊ ሀገራት ቡድን አባላት ጋር በትብብር እና በቅርበት ለመሥራት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት ገልጻለች።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: