በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮፕ-31 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው "ዝቅተኛ የካርቦን ኢኮኖሚን ለመገንባት ክህሎትን ማሳደግ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ማፋጠን" በተሰኘ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት ልማት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትሩ አቶ በረከት ፍስሃጽዮን እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በሰው ሀብት ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋፋት እና ፍትሐዊ የሆነ አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ይገኛል።
አዲሷን አስተናጋጅ አዲስ አበባን ለኮፕ-32 ጉባኤ ዝግጁ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት፣ የታዳሽ ኃይል ማፋጠን እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለወጣቶች በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደፈጠሩ እና አሁንም አዳዲስ አጋጣሚዎችን እየከፈቱ መሆናቸውን ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: