የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚመራበት የ5 ዓመታት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ ከአባላቱ ጋር ውይይት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው በተሰጠው የክትትልና ቁጥጥር ኃላፊነት መሠረት የተቋማት ዕቅድ እና አፈጻጸም ከሕግ እና አሠራር እንዲሁም ከስትራቴጂው ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ገልጸዋል።
አክለውም የተቋማቱን አፈጻጸም በቅርበት በመከታተል የዜጎችን ተጠቃሚነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
የኮሚቴው አባላት በተዘጋጀው ዕቅድ መሠረት የተሻለ አፈጻጸም እና የሥራ ዝግጁነት በማሳየት ኃላፊነታቸውን በጋራ እንደሚወጡም ሰብሳቢዋ አክለው ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የቋሚ ኮሚቴው የቀድሞ አመራሮች ባለፉት 5 ዓመታት ባከናወኗቸው ተግባራት ዙሪያ የነበራቸውን ልምድ ለአዲሶቹ አባላት ማካፈላቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: