ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በአቪዬሽን ትብብር እና የኢትዮጵያን የCOP32 ፕሬዚዳንትነት ለመደገፍ በሚደረገው አጋርነት ላይ መምከራቸውንም አመላክተዋል።
የጋራ ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማስፋት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የወል ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችል ፍሬያማ ምክክር አድርገናልም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: