ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከዚህ በፊት በG20 ጉባኤ ወቅት ባካሄድነው የሁለትዮሽ ስብሰባችን ወቅት የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት የተመለከተ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እና የጋራ ፍላጎቶችን በውይይታቸው ወቅት መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ይህም ፊንላንድ ኢትዮጵያ የምትረከበውን የCOP32 ፕሬዚዳንትነት ድጋፍ ጨምሮ፣ የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት የሰጠንበት ነው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: