Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 23

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከCOP31 መድረክ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ከንቲባዋ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃምፕተን ጋር ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ  በትብብር ዕድሎች እንዲሁም በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል።

ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን ሲሉም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

 

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: