Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራቁ ፕሬዚዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 94

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዚዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር መምከራቸውን አስታወቁ።

‎‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እንዲሁም በልማት ትብብር ረገድ የጋራ አቅም ያላቸውን ዘርፎች ወደ ውጤት የመቀየር ሥራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎‎በተጨማሪም በኢትዮጵያ የልማት ውጥኖች እና በጋራ ፍላጎት ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸው ጠቅሰው፣ በተግባር ላይ ለተመሰረተ ትብብር ጠንካራ ትሥሥር መገንባት ያለውን አስፈላጊነት በትኩረት መመልከታቸውን ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: