ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በውይይታቸው ወቅት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዚዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።
ውይይታችን ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሐሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም በተግባራዊ የትብብር መስኮች ወደፊት ለመራመድና አጋርነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር ያለንን የጋራ ፍላጎት ያንጸባረቀ ነው ብለዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: