Search

የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከክፍለ ከተሞች አመራሮች ጋር ተወያየ

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 94

የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከከተማዋ ክፍለ ከተሞች አመራሮች ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱን የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የከተማዋ ኮሪደር ልማት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፀጋዘአብ ኪዳኑ መርተውታል።

በመድረኩ የኮሪደር ልማቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ በሚኖረው ፋይዳ ላይ ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

መሰል ውይይቶች በቅርቡ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከነጋዴው ማኅበረሰብ፣ ከምሁራን እና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በተደረገው ውይይትም የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች የሚጀምረውን የኮሪደር ልማት ሥራ በከፍተኛ ጉጉትና ፍላጎት እየጠበቁት እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

በአስማረ ብርሃኑ        

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: