ዓለማችን እየበረታባት በመጣው የአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት ለከፋ ድርቅ፣ ለተደጋጋሚ ጎርፍ፣ ለከባድ አውሎ ነፋስ፣ ለሰደድ እሳት እንዲሁም ለመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተጋልጣለች።
የሙቀት መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ ሀገራት በከፍተኛ የሙቀት ማዕበል እየተመቱ የሰው ልጆች ህይወት አልፏል፤ በሰሜን እና ደቡብ ዋልታዎች የሚገኘው የበረዶ ግግር መቅለጥ ደግሞ የባሕር ወለል መጠን እንዲጨምር በማድረግ የባሕር ዳርቻ ከተሞችን የመስመጥ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ዳርጓቸዋል፤ ሌሎቹም በስጋት እንዲኖሩ ፈርዶባቸዋል።
ይህንን የበረታ የዓለማችንን ስጋት ለመግታት እና ምድራችን ከተጋረጠባት የህልውና አደጋ ለመታደግ እ.አ.አ በ1992 የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) ተመሰረተ።
ይህ ስምምነት ሀገራት የዓለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን መጨመርን እና የከፋ ጉዳቱን ለመግታት በጋራ የሚቆሙበትን መድረክ የፈጠረ ሲሆን፣ ስምምነቱን የፈረሙ ሀገራት በየዓመቱ የሚያደርጉት ስብሰባም የዓለም አቀፉ አየር ንብረት ጉባኤ (COP) በመባል ታወቀ።
ከ33 ዓመታት በዘለለው የኮፕ ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ ኢትዮጵያ ጉባኤው ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ እና የታዳጊ ሀገራት ድምፅ እንዲሰማ ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች።
ከጥያቄም አልፋ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም አረንጓዴ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ቀርጻ በመተግበር የጠባቂነት ትርክትን በመስበር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም አርዓያ ሆናለች።
*** ሙሉ መረጃውን ለማንበብ በአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ የሚገኘውን ሊንክ ይጫኑ።
በናትናኤል ጸጋዬ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: