Search

በ5 ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 252

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዝቡ በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንደሚረዱ ገልጸዋል፡፡

"ደረጃቸውን የጠበቁ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የመንግሥታቸው ዋና ትኩረት ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ፣ የሕዝብን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

አክለውም፣ "በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን የተገባውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥም ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: