👉 በሀገራዊ ምክክር የተገኙ የጋራ ምክረ ሐሳቦችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር እና በሕግ፣ በፖሊሲ እንዲሁም በተቋማዊ ማሻሻያዎች ለመተግበር መንግሥት ምን ዝግጅት እና የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል? በትግበራው ሂደትስ ከመላው ኢትዮጵያውያን እና ከኢትዮጵያ ወዳጆች ምን ይጠበቃል?
👉 ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ እና የነገ ዕጣ ፈንታዋን በጸና መሠረት ላይ ለመገንባት፣ የሀገራችን ረጅም ጊዜ ራዕይ የሆነውን «የመደመር ሥልጣኔ» ታላቅ ስትራቴጂ እየቀረጸች ትገኛለች። ይህንን ሀገራዊ ሥልጣኔ ለመገንባት በመንግሥት በኩል ምን ዝግጅት እንደተደረገ ቢገለጽ?
👉 የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ሲከተለው የነበረው ተግባር አፍራሽ እና አሉታዊ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያን ሰላም እና መረጋጋት ለማወክ አፍራሽ ኃይሎችን ሲደግፍ ቆይቷል። ከዚህ አንጻር የመደመር መንግሥት ለዚህ ተደጋጋሚ አፍራሽ ተግባር ያለው የፖሊሲ አቋምና የተግባር ምላሽ ምንድን ነው?
👉 የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት የሚፈታተኑ ድርጊቶችንስ እስከመቼ እንታገሳለን?
👉 የመደመር መንግሥት ሰላምን በድርድር፣ የሕግ የበላይነትን ደግሞ በጠንካራ አፈጻጸም በማረጋገጥ ሕዝባችንን የሚጠብቀውን ሰላም ለማስፈን የያዘው ተጨባጭ እርምጃ እና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥበት?
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: