የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፌደራል መንግሥቱ በሆደ ሰፊነት ተደጋጋሚ የሰላም ዕድሎችን ቢሰጥም ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን ግን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመፈፀም መከላከያ ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የተወያዩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን በውጭ ታሪካዊ ጠላቶች በሚመራው የጽምዶ ቡድንን በመቀላቀል ሀገር መውጋቱን ገልጸዋል።
በቀጣይ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዴት እንሥራ ለሚለው አቅጣጫ ለማስቀመጥ በዛሬው ውይይት መገኘታቸውን ጠቁመዋል።
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎችም በዚህ ወቅት ጦርነት ይብቃ ሰላም፣ ብልፅግና እና መረጋጋት ነው የምንፈልገው ብለዋል።
መሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት እንዲችሉ እንዲደረግ ነው መሻታችን ሲሉም ሐሳባቸውን በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
አሁን ለመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ መከፈልና የወደሙ መሠረተ ልማቶች መገንባት መጀመራቸውን የውይይቱ ተሳታፊዎች አድንቀዋል።
የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በአስማረ ብርሃኑ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: