Search

ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ተቋማት ለCOP32 ስኬት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የድርድር ውጤቶችን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ጥሪ ቀረበ

ቅዳሜ ኅዳር 05, 2019 121

የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ወደ COP32 በሚደረገው ጉዞ ላይ በአጋርነትና በድጋፍ ዙሪያ ከዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ መርተዋል።

ሚኒስትሯ በመድረኩ ላይ COP32 ለባለብዙ ወገን ትብብር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችንና ልማትን በተቀናጀ መንገድ ማስኬድ እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተዋል።

እስካሁን ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ አጋሮች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የበጎ አድራጎት ዘርፉ ከጉባኤው ዝግጅት ባለፈ የድርድር ውጤቶችን ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ እርምጃዎችና የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመቀየር ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎቹም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለጉባኤው እያደረገች ያለውን ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት በማድነቅ፣ ለCOP32 ፕሬዚዳንትነት አመራር አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠትና በቅርበት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: