Search

የኢሬቻ በዓል በጋምቤላ ተከበረ

ቅዳሜ ኅዳር 05, 2019 91

በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የኢሬቻ በዓል የተራራቀው የሚቀራረብበት የእርቅ፣ የምስጋና እና የአብሮነት በዓል በመሆኑ ሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦች ያለ ልዮነት በጋራ ያከብሩታል።

በየዓመቱ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፣ በጋምቤላ ከተማ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከብሯል።

የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች፣ ኢሬቻ በየዓመቱ በክልሉ መከበሩ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ሕዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን የወንድማማችነት እና የአብሮነት እሴት ይበልጥ እያጠናከረው መሆኑን ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልል የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ጋዶር ቾል፣ ኢሬቻ በክልሉ ሲከበር ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዓሉ የጋምቤላ እና የኦሮሚያ ሕዝቦችን ወሰን ተሻጋሪ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ እያጎለበተው ነው ብለዋል።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ዳግም አዳው በበኩላቸው፣ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ለማስቻል በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሚፍታህ አብዱልቃድር

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: