ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕእካተው ለወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ላስተላልፍ እወዳለሁ ብለዋል።
5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በ1ኛነት መምራታቸው፣ የኢትዮጵያን ጥልቅ የስፖርት ተሰጥኦ እና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርጋችሁ ማውለብለባችሁን እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ! ሲሉ መልዕእታቸውን አስተላልፈዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: