Search

የአየር ንብረት ትግበራ ድልድይ ስትራቴጂ ይፋ ተደረገ

ቅዳሜ ኅዳር 05, 2019 125

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር )፣ ሀገራት የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃ ቃል ኪዳኖቻቸውን በኢንቨስትመንት ሊደገፉ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶችና ተጨባጭ ተግባራት ለመቀየር የሚያግዝ የCOP31 ፕሬዚዳንሲ ውጤት የሆነውን የአየር ንብረት ትግበራ ድልድይ (Climate Implementation - BRIDGE) ይፋ የማድረግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።

በይፋዊ ማስጀመሪያው ላይ ከBRIDGE የመጀመሪያ ቡድን አባል ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የብዙ ወገን የልማት ባንኮች (multilateral development banks) ተወካዮች በመገኘት ፕሮግራሙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮችና በጋራ ቁርጠኝነቶች ላይ ስትራቴጂያዊ ውይይት አካሂደዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሯ የሀገራትን የአየር ንብረትና የልማት ቅድሚያ ጉዳዮች ከፋይናንስ፣ ከኢንቨስትመንትና ከቴክኒክ ድጋፍ ጋር ማገናኘት ትግበራን ለማጠናከር ያለውን አስፈላጊነት አጉልተው ገልጸዋል። ለኢትዮጵያም እንዲህ ያለው ትብብር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባለው የተልዕኮ ደረጃና በተግባራዊ አፈጻጸም መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ፣ ብሔራዊ ዕቅዶችን ወደ ኢንቨስትመንት ዕድሎችና ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር ይረዳል።

ውይይቱ ከCOP31 በኋላም የሀገራትን በትብብር የሚመራ አተገባበር ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከአጋር አካላት ጋር ሐሳብ ለመለዋወጥ ዕድል ፈጥሯል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: