Search

"የአየር ንብረት ጥበቃን ከብሔራዊ ልማት ጋር ማቀናጀት ወሳኝ ነው" - ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ኅዳር 05, 2019 100

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ በአንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን በተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፈው ንግግር አደረጉ።

ሚኒስትሯ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለተሳታፊዎች ያካፈሉ ሲሆን፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችን ከብሔራዊ የልማት አጀንዳ፣ ከኢንቨስትመንት እና ከኢኮኖሚያዊ የመቋቋም አቅም ጋር በተቀናጀ መንገድ የማስፈጸምን አስፈላጊነት በሰፊው አብራርተዋል።

የአየር ንብረት ጥበቃ ቁርጠኝነቶችን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየር የፋይናንስ ሚኒስቴሮች የአየር ንብረት ቅድሚያ ጉዳዮችን ከብሔራዊ በጀት፣ ከመንግሥት ኢንቨስትመንት እና ከፋይናንስ ስትራቴጂዎች ጋር በማቀናጀት ወሳኝ ሚና መጫወት እንዳለባቸውም አጉልተው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከተቀመጡ ግቦች እና ዕቅዶች ወደ ተጨባጭ ኢንቨስትመንትና የልማት ውጤቶች ለመሸጋገር ፖሊሲዎችን፣ ተቋማዊ አቅምን፣ የፋይናንስ ሀብቶችን እና የትብብር አጋርነቶችን በተቀናጀ መንገድ ማስኬድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: