የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ ከካናዳ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትር ጁሊ ዳብሩዚን ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ትብብርና አጋርነትን ስለማጠናከር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቋቋም፣ የአየር ንብረት መቋቋም አቅምን ለማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በጋራ የተለዩ ቅድሚያ ጉዳዮችን ለማራመድ ትብብርን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የCOP32 ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጧል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: