በመቐለ ከተማ ለአንድ ወር የተሃድሶ ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል።
በትግራይ ክልል ከ47 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ለተሃድሶ ሥልጠና መመዝገባቸው ይታወቃል።
ከእነዚህም ውስጥ ለአንድ ወር ሥልጠና ላይ የቆዩት የቀድሞ ታጣቂዎች ናቸው ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁት።
የተሃድሶ ሥልጠናውን ያጠናቀቁት እነዚህ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉ ይሆናል።
ሌሎች የቀድሞ ታጣቂዎችንም በቀጣይ በተጠናከረ መንገድ ወደ ተሃድሶ ሥልጠና የማስገባት ሥራው እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አወሎ አብዲ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የባለአደራ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።
በአስማረ ብርሃኑ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: