ከአዲስ አበባ ከተማ 640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የቦረና ብሔራዊ ፓርክ፣ በደቡባዊ ኦሮሚያ ዞን በሰፊ መልክዓ ምድሩ እና በበለጸገ የዱር እንስሳት ሀብቱ የኢትዮጵያ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው።
የመደመር መንግሥት የቱሪዝም ዘርፉን ከኢኮኖሚው ዋና ምሰሶዎች አንዱ በማድረግ የተፈጥሮና የባህል ሀብቶችን ለማልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ እንደ ቦረና ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ያልተነኩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የመጠበቅና የማስተዋወቅተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
6 ሺህ 700 ካሬ ኪሎ ሜትር ገደማ ስፋት ያለው ፓርኩ በአምስት ክላስተሮች የተደራጀ፣ የበለጸገ የብዝኃ ሕይወት መገኛ ነው። በውስጡ 4 ብርቅዬ ዝርያዎችን ጨምሮ 64 አጥቢ እንስሳትን እንዲሁም 286 የአዕዋፍ እና 1 ሺህ የዕፅዋት ዝርያዎችን ይዟል።
አንበሳ፣ ጎሽ፣ ቀጭኔ፣ የሜዳ አህያ፣ አጋዘን፣ ሚዳቋ እና ሰጎንን ጨምሮ የተለያዩ የዱር እንስሳት የተፈጥሮ መኖሪያ የሆነው ፓርኩ በየዓመቱ ከ5 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ያስተናግዳል።
በመደመር እሳቤ በተከናወነው ሥራ የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል ይህን ውድ የተፈጥሮ ቅርስ መጠበቅና ማልማት ለአካባቢው ማኅበረሰብ የኢኮኖሚ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የሚከበረውን 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አምክንያት በማድረግ ከምክር ቤቱ እና ከመገናኛ ብዙኃን የተውጣጣ ቡድን የቦረና ብሔራዊ ፓርክን እና የሳሪቴ ክላስተርን ጎብኝቷል።
በብርቱካን አስናቀ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: