Search

ብልጽግና ፓርቲ እና የሩስያው ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ የተፈራረሙት የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት

ሰኞ ኅዳር 07, 2019 105

የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነቱን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እና የ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ጸሐፊ እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ቭላድሚር ያኩሼቭ ፈርመውታል።

“ለሕዝቦች ነፃነት!” ከተሰኘው ሩስያ መራሽ የፓርቲዎች የጋራ ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በሞስኮ የተፈረመው ስምምነት፣ ከዓድዋ ድል ጀምሮ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የሩስያ ታሪካዊ ወዳጅነት እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ አጋርነት ወደ ላቀ ተቋማዊ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ነው።

ስምምነቱ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን መሠረት በማድረግ በፓርቲ ግንባታ፣ በልማት ልምዶች እና በተቋማዊ ግንኙነቶች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች በጋራ በመሥራት ብሔራዊ ሉዓላዊነትን የሚያስከብሩበት፣ ዘመናዊ የቅኝ አገዛዝ ተጽዕኖዎችን የሚከላከሉበት፣ የባለብዙ ወገን ትብብርን የሚያጠናክሩበት እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነት የሚያሳድጉበት እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ ስምምነት ከመደበኛ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ተጨባጭ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥ ስትራቴጂያዊ ትብብር የሚያሸጋግር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑም ነው የተገለጸው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: