Search

የአጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ አቶ ጌታቸው ረዳ ጥሪ አቀረቡ

ሰኞ ኅዳር 07, 2019 109

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በህገ ወጡ የህወሓት ቡድን አጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በመቐለ የተሃድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠና ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ላይ በተገኙበት ወቅት ነው።

ሥልጠናውን ካጠናቀቁት ከ16 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ከኮር አመራር እስከ ሻለቃ ማዕረግ የነበራቸው መሆኑን አቶ ጌታቸው በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

እነዚህ በትጥቅ ትግል የነበሩ ዜጎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በተሃድሶ ሥልጠና ማለፋቸው ለትግራይ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላ ሀገራችን ሰላምና መረጋጋት የሚኖረው ፋይዳ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በቀጣይም መንግሥት የተሃድሶ ሥልጠና የመስጠት ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አሁንም በህገ ወጡ የህወሓት ቡድን አጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሥልጠናው የማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣  የሥራና ክህሎት ሚኒስትሩ አወሎ አብዲ፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የባለአደራ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

በአስማረ ብርሃኑ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: