Search

አዲስ አበባ በተለይ በህጻናት መዝናኛ ረገድ በአጭር ጊዜ ያከናወነችው የአካቶ ትግበራ ሥራ አርዓያነት ያለው ነው - የጀርመኗ ላይፕዚሽ የልዑካን ቡድን አባላት

ሰኞ ኅዳር 07, 2019 98

አዲስ አበባ በአካታች የከተማ ልማት ሥራዎች ያላትን ተሞክሮ ለጀርመኗ እህት ከተማ ላይፕዚሽ የምታጋራበት የልምድ ልውውጥ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመዲናዋ አስተዳደር ሴቶችና ወጣቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በልማት፣ በትምህርትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ የአካቶ ትግብራ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

አዲስ አበባ ባለፉት አምስት ዓመታት ስማርት ሲቲ ለመገንባት ባከናወነቻቸው የአካቶ ትግበራ ሥራዎች ሴቶችን፣ ህጻናትን፣ ወጣቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሏን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የአዲስ አበባ እና የጀርመኗ ላይፕዚሽ እህትማማች ከተሞች የሁለትዮሽ ግንኙነት ለዓመታት የዘለቀ ሲሆን፣ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የልምድ ልውውጥ በማድረግ በጋራ የከተማ ልማት እሴቶች ላይ በትብብር መስራት ጀምረዋል።

የጀርመኗ እህት ከተማ ላይፕዚሽ የልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ለውጥና በተከናወኑ ሥራዎች መደነቃቸውን ገልጸው፣ የአዲስ አበባ ተሞክሮ ወደ ከተማቸው ሲመለሱ ለተለያዩ ሥራዎች ግብዓት እንደሚሆናቸው መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

የላይፕዚሽ የአካቶ ባህል ትምህርት ዳሬክተር ጃና ዘህለ እንደገለጹት፣ አዲስ አበባ በኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት በተለይ በህጻናት መዝናኛ ረገድ በአጭር ጊዜ ያከናወነችው የአካቶ ትግበራ ሥራ አርዓያነት ያለው ነው ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: