ልዑካኑ በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ መቐለ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና ሌሎች የባለአደራ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልኡካን ከዛሬ ኅዳር 8 ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ኦፊሴላዊ የሥራ ጉብኝት በመቐለ ከተማ ያካሂዳሉ።
ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሰብአዊ ዕርዳታ፣ ተፈናቃዮች፣ የዲዲአር (የትጥቅ የማስፈታት፣ የዲሞቢላይዜሽን እና የመልሶ ማቋቋም) ሂደት እንዲሁም የክልሉ ሰላም ጉዳይ ውይይት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።
በአስማረ ብርሃኑ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: