የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ ቡድን ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
ከንቲባዋ እስካሁን በከተማው የውኃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ማስፋፊያ እና ማሻሻያ፣ በፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም በትራንስፖርት እና በሌሎች ቁልፍ የልማት ዘርፎች ከዓለም ባንክ ቡድን ለተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ትብብሩን በማስፋት፣ አዳዲስ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ እና በመተግበር ለከተማዋ ዘላቂ ልማት እና ለነዋሪዎቿ የተሻለ ኑሮ በጋራ ለመሥራት ከተስማሙበት አዎንታዊ ውይይት በኋላ፣ የሁለቱን አካላት ትብብር ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: