Search

የተመድ ልዑካንና አምባሳደሮች በመቐለ የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከልን ጎበኙ

ረቡዕ ኅዳር 09, 2019 137

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከል ዛሬ ጎብኝተዋል።

ከትናንት ጀምሮ በትግራይ ክልል የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ልዑካኑ፣ ከክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎችም የመስክ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን፣ የዛሬው የተሃድሶ ማዕከል ጉብኝትም የዚሁ ተልዕኮ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ልዑካኑ ከባለአደራ አስተዳደሩ ጋር በትኩረት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉበት አግባብ ይገኝበታል።

በውይይቱ ወቅትም ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማቱ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንን ሥራ በማድነቅ፣ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከሉን መጎብኘታቸውም በቀጣይ ከኮሚሽኑ ጋር ያላቸውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል።

በአስማረ ብርሃኑ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: