Search

በኢትዮጵያ የተመዘገቡ አዳዲስ የልማት ሥራዎችን ታሳቢ ያደረገ የ'ጂዲፒ' አለካክ ሥርዓት መተግበር አስፈልጓል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ኅዳር 17, 2019 43

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ የተመዘገቡ አዳዲስ የልማት ሥራዎችን ታሳቢ ያደረገ የ'ጂዲፒ' አለካክ ሥርዓት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ለዚህም የዲጂታል ኢኮኖሚን ለአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከለውጡ በፊት የሞባይል ገንዘብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደማይታወቅና ዛሬ ላይ በትሪሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ አብራርተዋል።

ይህንን ዕድገት ታሳቢ ያደረገ የ'ጂዲፒ' አለካክ ሥርዓት ስላልነበረ መልሶ ማየት እንዳስፈለገም አስገንዝበዋል።

ከለውጥ በፊት ከተሞች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስላልነበሩ፣ አሁን በከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ መሠረተ ልማት ለመገንባትና ሥራ ለመፍጠር እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የሚለካ ሥርዓት እንዳልነበረ አስታውሰዋል።

በግብርናው ዘርፍ አርሶ አደሮች መሬቶቻቸውንና ጉልበታቸውን ደምረው የተሻለ ምርትና ምርታማነት የሚያገኙበት የክላስተር አሠራር ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል።

ሆኖም በነበረው አለካክ በእያንዳንዱ ማሳ የሚገኘውን ምርት ለማወቅ በቂ ቆጠራ ማካሄድ ይፈልግ እንደነበር አመላክተዋል።

በተመሳሳይ በሌማት ትሩፋት ዘርፍ በተለይም በዶሮ፣ በእንቁላል እና በወተት ምርት ከፍተኛ እመርታ ቢመዘገብም፣ ይህንን አዲስ አሠራር የሚለካ ሥርዓት እንዳልነበረ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

በኢንዱስትሪው ዘርፍም ከለውጥ በፊት በመንግሥት የነበሩ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በሀዋሳ፣ በኮምቦልቻ እና በመቐሌ የሚገኙ ሦስት ብቻ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅት ግን በመንግሥት እና በግል ከ15 በላይ ትላልቅ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች መገንባታቸውን ጠቁመዋል።

በአድማሱ አራጋው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: